ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Search Results

Nested Applications

Asset Publisher

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Fri, 8 Mar 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Tue, 27 Feb 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Wed, 21 Feb 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ Mon, 12 Feb 2024

Asset Publisher

Asset Publisher

null ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም )

የጉምሩክ ኮሚሽን ከየካቲት 1 እስከ 7 /2016 ዓ.ም  ባደረገው ክትትል 188 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 87 ነጥብ 1  ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 275 ነጥብ 6 ሚሊዮን  ብር የሚያወጡ  የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት  እና የተለያዩ  ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር  ድሬድዋ፣ አዳማ  እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 67 ሚሊዮን፣ 55 ሚሊዮን እና42  ሚሊዮን  ብር   የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን ኮንትሮባንዱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ስድስት  ተጠርጣሪዎች እና ሶስት ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

 

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

ጠቃሚ መረጃዎች