Asset Publisher

null ”የወደብ ስምምነቱ አስፈላጊው ሁሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት፣ የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ህጎችን ባገናዘበ መንገድ የተፈጸመ ነው “ ፡- የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ታህሳስ 24 ቀን 2016 ዓ.ም)

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የፈረሙትን የወደብ ስምምነት አስመልክቶ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እና አመራሮች ለስምምቱ ያላቸውን ድጋፍ እና ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተዘጋጀው የደስታ መግለጫ ስነስርዓት ላይ መልእክት ያስተላለፉት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጸመው ስምምነት በድንገት የመጣ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራበት የነበረ እና የሪፎርሙ አንዱ አካል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

”ኢትዮጵያ ያላትን ህዝብ ብዛት እና የመልማት ፍላጎት የሚመጥን ወደብ ያስፈልጋል ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ“ ውሳኔው የህዝብን የዘመናት ጥያቄ የመለሰ እና የመጭውን ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወስን መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኮሚሽነር ደበሌ አክለውም የወደብ ስምምነቱ አስፈላጊው ሁሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት፣ የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ህጎችን ባገናዘበ መንገድ የተፈጸመ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በጅቡቲና በታጁራ ወደቦች ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን በመክፈት ለገቢ እና ወጭ ዕቃዎች የጉምሩክ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የተፈረመው ስምምነት ለጉምሩክ አገልግሎት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የኮሚሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በበኩላቸው የተደረሰው ስምምነት ታሪካዊና ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ያላትን የዲፕሎማሲ ከፍታ የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission