የጉምሩክ አስተላለፊነት ስልጠናን ይመለከታል፤

Search Results

Nested Applications

Asset Publisher

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Fri, 8 Mar 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Tue, 27 Feb 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Wed, 21 Feb 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ Mon, 12 Feb 2024

Asset Publisher

Asset Publisher

null የጉምሩክ አስተላለፊነት ስልጠናን ይመለከታል፤

ማስታወቂያ

የጉምሩክ አስተላለፊነት ስልጠናን ይመለከታል፤

ለአዳዲስ የጉምሩክ አስተላላፊዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የ3ኛ ዙር የጉምሩክ አስተላፊዎች ስልጠና ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት (እሁድን ጨምሮ) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በመሆኑም ለ3ኛ ዙር ስልጠና በክልሎች በኩል የተመዘገባችሁና ከዚህ በፊት በማስታወቂያ መሰረት ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ተመዝግባችሁ ለ3ኛ ዙር የተመረጣችሁ በሚከተለው ቅደም ተከተል መሰረት ምዝገባ በማድረግ ወደ ስልጠና የምትገቡ ይሆናል፡፡

እነዚህም፡-
1ኛ. በመጀመሪያ ከክልሎችና ከአዲስ አበባ ለስልጠና የተመረጣችሁ መሆኑን ስማችሁን ECC CUSTOMER SERVICE DIRECTORET ተብሎ በተከፈተ የጉምሩክ ኮሚሽን የቴሌግራም ገጽ ወይም በሚከተለው ሊንክ https://t.me/+MQ_UOoFsoYIzNGU0 ለዚህ ስልጠና በተከፈተ የቴሌግራም ገጽ በመግባት ስማችሁ መኖሩን ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል፤
2ኛ. በመቀጠል የኦን ላይን ምዝገባ (Online Registration) ማድረግ የሚጠባቅባችሁ ሲሆን ቀጥሎ የተገለጸውን ሊንክ https://forms.gle/bbgrx3QTjhvrWrQCA በመጫንና ቅጹን ኦንላይን ሞልታችሁ መላክ ይጠበቅባችኋል፤
3ኛ. የስልጠናውን ክፍያ በቴሌግራም ገጹ ፖስት ከተደረጉ የክፍያ አማራጮች ውስጥ አንዱን በመምረጥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ኦፍ ኮሜርስ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000002565173 ክፍያ መፈጸም፤
4ኛ. የስልጠና ክፍያ የተፈጸመበትን ደረሰኝ፣ የመጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ማስረጃ፣ መታወቂያ ኮፒ በመያዝ ከላይ በተጠቀሰው ቀን በስልጠና ቦታ መገኘት፤
የስልጠና ቦታ
-  አልጋ (Dormitery) ለምትይዙ ስልጠናውና የዶርም አገልግሎት የሚሰጠው 6 ኪሎ አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ሲሆን እሁድ በ26/10/2014 ገብታችሁ ማደር ይጠበቅባችኋል፤

-  አልጋ (Dormitery) ለማትይዙ ስልጠናው ሜክሲኮ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የንግድ ስራ ት/ቤት (School Of Commerce) ሲሆን በ27/10/2014 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ስልጠናውን፤

በተጨማሪ ተጠባባቂ ተብሎ ስማችሁ የተጠቀሳችሁ ወደ ስልጠና እንድትገቡ ከቢሮ እስከሚደወልላችሁ ድረስ የኦን ላይን ምዝገባና ክፍያ እንዳትፈጽሙ፤

ስለስልጠናው የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ECC CUSTOMER SERVICE DIRECTORET ወይም  Round 1 Customs Clearing Agent Training ተብሎ በተከፈቱ የቴሌግራም ገጽ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
                                                                የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

ጠቃሚ መረጃዎች