Asset Publisher

null የጉምሩክ ቀረጥና ታክስን በቴሌ ብር ለመክፈል የሚያስችል የማስጀመሪያ ስነስርዓት ተከናወነ

የጉምሩክ ቀረጥና ታክስን በቴሌ ብር  ለመክፈል የሚያስችል የማስጀመሪያ ስነስርዓት እና ስምምነት በጉምሩክ ኮሚሽን እና በኢትዮቴሌኮም መካካል ተፈጽሟል፡፡


ስነስርዓቱ  የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በተገኙበት በዛሬው እለት በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ተከናውኗል፡፡


በስምምነቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ደበሌ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን በሁለንተናዊ መልኩ ዘመናዊ ለማድረግ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ  በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው በዚህም የገቢ እና የወጭ ንግዱ የተሳለጠ እንዲሆን እና በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ እንግልቶችን መቀነስ እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡


የጉምሩክ አገልግሎት በባህርይው ውስብስብ እና በርካታ ተዋናዮች ያሉበት መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነር ደበሌ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወረቀት አልባ እንዲሆኑ ማድረግ ዘመኑ የሚጠይቀው ዋና ተግባር እንደሆነም አስረድተዋል፡፡


ኮሚሽነር ደበሌ  አክለውም ፣ ደንበኞች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስን በቴሌ ብር እንዲከፈሉ መደረጉ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ እንደሆነ ተናግረው በክፍያ ሂደት የሚያጋጥሙ  በርካታ ችግሮችን ለመቀረፍ ፣የአገልግሎት አሰጣጥን ተደራሽ ለማደረግ እና  የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ እንዲሆን ያስችላልም ብለዋል፡፡


የጉምሩክ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ በበኩላቸው፣ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የኮሚሽኑን አገልግሎት ለማዘመን የህግ ፣ የአሰራር እና የቴክኖሎጂ ማሻሻዎች መደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡


የወረቀት አልባ የጉምሩክ አገልግሎት፣የአንድ መስኮት አገልግሎት እና የካርጎ ፍተሻ ስርዓት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተግባራዊ የሆኑ ዋና ዋና የሪፎርም ስራዎች መሆናቸውንም  ጠቁመዋል፡፡


የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በቴሌብር መከናወኑም የንግድ ስርዓቱን ለመሳለጥ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ፣ የክፍያ ሰንሰለቱንም በማሳጠር  ጊዜና ወጭን በመቀነስ ፋይዳው የጎላ እንደሆነም አቶ አዘዘው አስረድተዋል፡፡


የኢትዮቴሌኮም ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ኢትዮቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማደረግ እየሰራ መሆኑን ተናግረው ከመደበኛ አገልግሎት ባሻገር በኢኮኖሚው ዘርፍ ውጤት ማምጣት የሚያስችሉ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተግባራዊ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡


ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር የተደረገው ስምምነትም በቴሌ ብር አማካይነት  የጉምሩክ ቀረጥና ታክስን በፍጥነት ፣ በየትኛውም ቦታ ያለምንም እንግልት ለመክፈል የሚያስችል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡


የጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

 

Asset Publisher