የኢትዮጵያ ማህጸን ጀግኖችን ከመውለድ ነጥፎ አያውቅም፡፡ በየዘመኑ ህዝብን ከጥፋት፤ ሀገርን ከመበተን ያዳኑ አያሌ ጀግኖች በሁሉም የትግል አውድማ ተፈጥረዋል፡፡ በተለያዩ የጦርነት አውደውጊያዎች ፣በህክምናው ዓለም፣ በፖለቲካው መስክ፣ በኢኮኖሚው ግንባር እና በሌሎችም መስኮች ሀገራችን ስመ ገናና ሆና ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር ያደረጉ አያሌ ታሪክ ሰሪዎች ነበሯት፣ ዛሬም እንዲሁ፡፡ ዛሬም በእኛ ዘመን አሸባሪው እና ዘራፊው የህዋሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የከፈተውን ጦርነት ለመመከት እየተደረገ ባለው ትግል ጠላትን ድባቅ የሚመቱ የጦር ጀግናዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ በሌሎችም የሙያዎች ፈርጆችም በርካታ ጀግኖች ተፈጥረዋል፡፡ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ኤርምያስም በአሁኑ ትውልድ እንደ አጥቢያ ኮከብ እያበሩ፣ ህዝብን ከጨለማ ወደ ብርሀን እየመሩ አስቸጋሪዎቹን የመከራ ቀናት ማሻገር የቻሉ ታላቅ አባት ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ብጹእነታቸው፣ምትክ በሌላት በነፍሳቸው ተወራርደው ህይወትን አትርፈዋል ፣ የኃይማኖት ልዩነት ሳይገድባቸው ለሁሉም የልግስና እጃቸውን ዘርግተዋል፡፡ ስለሆነም ለእኒህ ሰው በሌለ ቀን ሰው ሁነው ለተገኙት፣ የልዩነት አጥር ሳይገድባቸው ውለታ ለሰሩልን የዘመናችንን ጀግና ማክበር እና እውቅና መስጠትም ተገቢ ነው፡፡ አሸባሪው የህዋሃት ቡድን በወልድያ ከተማ በቆየባቸው ቀናት የግለሰብ ቤትን ጨምሮ መንግስታዊ ተቋማትን ዘርፏል ፣አውድሟልም፡፡ ትንሽ እፍረት እና ርህራሄ ያልፈጠረበት አሸባሪው ህዋሃትም እንደለመደው የብጹእ አቡነ ኤርምያስን ተሽከርካሪ መዝረፉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጉምሩክ ኮሚሽንም 6.7 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ተሽከርካሪ ለብጹእ አቡነ ኤርምያስ በስጦታ አበርክቷል፡፡ በድጋፍ ርክክቡ ንግግር ያደረጉት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፣ አቡነ ኤርምያስ የሰሩት ታላቅ ገድል ራስን ለህዝብ መስጠት ክብርን የሚያጎናጽፍ መሆኑን ያስመሰከረ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ ውለታቸውንም ሀገር የማትረሳው፤ትውልድም የማይዘጋው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ድጋፉን የተረከቡት ብጹእ አቡነ ኤርምያስም፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በሰሜን ወሎ ዞን ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች 30 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ምግብ ነክ ቁሳቁስ እና የተለያዩ አልባሳቶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ንግግር ያደረጉት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ፣ ኮሚሽኑ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑ በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ እና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በተቻለው አቅም ተደራሽ ለመሆን ጥረት እያደረገ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነር ደበሌ፣ ከለውጡ ወዲህም ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮች በወልድያ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡ ሲሆን ሲሆን 30 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚያወጡ፤ 500 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት፣ ሩዝ ፣ፓስታና ሌሎች ምግብ ነክ ቁሳቁሶች እና አልባሳት ለዞኑ አስረክበዋል፡፡ ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ወሎ አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል በበኩላቸው፣ ለዞኑ የተደረገው ድጋፍ ኮሚሽኑ እውነተኛ የህዝብ ተቋም መሆኑን ያስመሰከረበት ተግባር መሆኑን ገልጸው ድጋፉ ለተጎጅዎች በወቅቱ እና በትክክል እንዲደርስ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ ተገኝተዋል፡፡
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ እና ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች በቁጥጥር ስር ዋሉ:: በወቅታዊው የገበያ ዋጋ 12 ሚሊዮን 350 ሺህ ብር የሚያወጡ እና በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ አምስት የወርቅ ጥፍጥፎች በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የወርቅ ጥፍጥፎቹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ማእከል (NISS) በሰጠው ጥቆማ መሰረት የተገኘኙ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ ላይም የፌደራል ፖሊስ ምርምራ እያደረገ ይገኛል። ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ የኮንትሮባድ እቃዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉም ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ሲሆን ለዚህ ስራ ስኬታማነት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ማእከል፣ የፌደራል ፖሊስ ኤርፖርት ዲቪዥን እና የአየር መንገድ ደህንነት መስሪያ ቤት ያበረከቱት አስተዋጥኦ ከፍተኛ ነው ፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል የጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን የስተላልፋል::
ከ84 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ባሳለፍነው ሳምንት ከ84.3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 78.4 ሚሊዮን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 5.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡ የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ ፣ ድሬድዋ እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 18 ሚሊዮን 998 ሺህ፣ 18 ሚሊዮን 987 ሺህ ሚሊዮን እና 17.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆኑ የኮንትሮባንድ እቀቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡ የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ከ72 ሚሊዮን 100 ሽህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 68 ሚሊዮን 661 ሺህ ብር በላይ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 3 ሚሊዮን 439 ሺህ ብር የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡ የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ጅግጅጋ ፣ አዳማ እና ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 16.6 ሚሊዮን፣ 14.3 ሚሊዮን እና 12.7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ናቸው፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡ የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Today 2 Yesterday 12 Week 14 Month 278 All 11859

Currently are 14 guests and no members online