Asset Publisher

null ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም)

የጉምሩክ ኮሚሽን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህ የግምገማ መድረክ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው በገቢ አሰባሰቡ የተመዘገበው ውጤትም ስኬታማ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

በ2016 የመጀመሪያው ግማሽ የበጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ አርእስቶች 103 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ የነበረ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ  97 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ገልፀዋል፡፡

ገቢው የተሰበሰበው ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከሌሎች ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ነው ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ ካለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም በ9.9 ቢሊዮን ብር (11.42 በመቶ) ብልጫ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
የኮሚሽኑ የስትራቴጂክ ፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ዱፌራ የኮሚሽኑን የ2016 ግማሽ በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Asset Publisher